Zone9_Bloggers2015(Oromedia) — ይድረስ የአንድነት ደጋፊ ነን ባይ የጠባብ ኢትዮጵያዊነት ልክፍተኞች ስለአንድ ኢትዮጵያ ሰባኪዎች እኔ የብሄር ብሄረሰብ ጥላቻ የለብኝም። ከማንኛውም ብሄር ሀይማኖት ለሀገሩ ትልቅ መስዋዕት የከፈለ ለኔ ጀግና ነው።

ሆኖም ግን አንድ ግለሰብ የኦሮሞ መገለጫ የሆነን ነገር ሲጠቀም ስለምን ያወግዙትና የጥላቻ ስድቦች ይሰነዝሩበታል? ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት ነው የጋራ ማንነት የገነባች ሁሉም የእኔ እማማ ኢትዮጵያ ብሎ ዳር ድንበሯን አስከብሮ ህልውናዋ ተጠብቆ የምትዘልቀው ?

በብሄር አናምንም ይሉና ስለራሳቸው የወጡበት ብሄር ግን ታላቅነት ጀግንነት የታሪክ ሀፍታምነት ሲሰብኩን ይቆዩ እና ግና የኦሮሞ ልጅ ግና ኦሮሞ ሲል ይናደዳሉ። የኦሮሞ ስም ሲያዩ ስሙን እንዲቀይርላቸው ሁሉ በረዘመ ምላሳቸው ያንጓጥጣሉ ወይሥ ብሄርን መጥራት ለናንተ ብቻ ይፈቀዳል ?

እኔ የሌላውን ብሄር ሳልቃወም አክብሬ የራሴን ባህል ቋንቋ ታሪክ ብናገር በሚሴጅ በኮመንት ማንነቴን በተመለክተ በሥድብ አጠገቡኝ ዘረኛ ጠባብ የሚል ታርጋ ለጠፉብኝ አሜን ብዬ ተቀበልኩ ።

befekeእውነት እንነጋገር እናንተ ድሮም,,,,,,,,,!ኦሮሞን የሚሠድቡና የሚያብጠለጥሉ ሰዎች ዝምብዬ ሣስባቸው በራሳቸው ትምክተኛ የዘረኝነት አንቡላ ሰክረው እብደት ውስጥ የገቡ ፣በኦሮሞ ማንነት የቅናት ዛር አናታቸው ላይ ወጥቶ የሚጋልባቸው ፣በቃ ምክንያታዊ ያልሆኑና በስማበለው ብቻ የሚነዱ በስጥ እንግዲ ተረት የእውቀት ማማ ላይ የደረሱ ከነሱ ውጭ ምንም አዋቂ ያለ የማይመስላቸው መውጫ መግቢያ አጥተው የሚኳትኑ ገልቱ ልበቢሶች ይመሥሉኛል!።

ያስተውሉ! የዛሬዋ ኢትዮጵያ ለትምክህተኝነት የሚን ጥግ የላትምና ከትምክህተኝነት ይፅዱ! ታሪክን ጠንቅቀው የሚያውቁ,,,,,,,,,! እውነትን አለምን የሚያጠኑ የተማሩና የተመራመሩ,,,,,,,”እንዲ”ያነሡታል በክብሩ በቁም ነገሩ! ኦሮሞነቴን ዝም ብዬ ሣሥበው ደስታ መላ አካላቴን ይወረዋል ኡፍ በቃ ሲያረካ!!!!!!!!!

ኦሮሞ አባቴ፤እናቴ፤አያት ቅድመ አያቴ,,,,,,,,,,!ዘር ሀረግ ማህፀን እትብቴ ኩራት ማንነቴ ከምንም የማላነፃፅረው,!ብልጫ ማንነቴ ደስታ ፍስሃዬ የሥከለት ሞቴ በቃ ኦሮሞነቴ ! ጠባብ ዘረኛ መባሌ ካልቀረ እደዚ እርፍ በሉ!

15 thoughts on “ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት የጋራ ማንነት ይገነባል?

 1. Guma,u must be stupid do not try to change the main subject or run away from the truth.The writer is telling you the fact what is going in the country.

 2. @Guma.

  I do not see the rainbow here…may be go look some where …you will recognize when you see it. Defiantly Green, red and yellow are in it…certainly none of the one they clothing

 3. May God bless you brother! You put it right.The only enemy of Ethiopia and its people is the extremist few who call themselves true Ethiopians.They are the most ethnocentric and cancerous hate group . Especially the old elite group.

 4. I don’t know if this piece of writing is intended to appease the formation of unity among Southern nations of that damn country and at the same time criticize the G-7’s. But, anyhow, I think it is very early to do so. No one one knows what would happen to PAFD in the long run. Because, it is very hard to predict even the fate of one homogeneous organization/party, let alone these heterogeneous make up party….. God help us, anyway!

  1. Tolcha, I think this is simple to understand. This is nothing to do with what you are talking about. I think you wanna divert attention. Shame on you!

 5. guma u are stupid u are not living but existing object!bloody bastard!
  we always proud be an oromo without ofending and descriminatiing
  any society.
  guma dont forget we are in 21st century
  dont comment rubbish if u upset bad luck bilissummaa is near by u understand u mourn
  guy!!!!!!
  g3
  IUO

 6. The gentle man and the lady in the picture did not exressly say any thing about their ethnicity. They simply wore the scarf which happen to have similar colors as the flag of the TPLF-dominated current Oromia State. I guess they might have got that scarf from the prison. It may be produced by inmates, who are vastly oromo political prisoners. The two in the picture wore it in memory of their prison time or in solidarity with the Oromo prisoners or other reasons. Why is this such a big deal?

 7. ከሁሉም በፊት ይህንን ኣስተያየት በኣማርኛ ለመጻፍ የቻልኩት ቋንቋ መግባቢያ በመሆኑና የሚመለከታቸው እንዲገነዘቡት ነው!
  ስለኦሮሞ ማንነት ሲነሳ ኣንዳንዶች ኩራት ሲሰማቸውን ውስጣቸው በደስታ ሲሞላ ሌሎች ደግሞ እርር-ድብን ብለው መንጨርጨራቸውና የስድብ ናዳ ላማውረድ ሲጣደፉ መስተዋሉ ከበስተጀርባው ሚስጢር ስለመኖሩ ያመለክታል።
  ከሁሉም በፊት ስለኦሮሞነት ለመናገርና የኦሮሞን ማንነት ለመግለጽ ከ’ኢትዮጵያዊነት’ ጎራ ፈቃድ ኣልያም ቡራኬ የሚያስፈልግ ኣይመስለኝም።
  የኦሮሞ ህዝብ በማንነቱ መገለጫ እሴቶች እንደሚኮራ ሁሉ ሌላውም ብሄር፡ ህዝብ ስለማንነቱ ኣንገቱን ቀና ኣድርጎ ቢናገርና ቢያንጸባርቅ ሊያንጨረጭረን ኣይገባም። በኣንጻሩ ያቺን ‘ሃገር’ ከገባችበት ኣጣብቂኝ ለማላቀቅና በውስጧ ያሉ ህዝቦች በሁሉም ኣንጻር ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ምኞትና ፍላጎቱ ያለው ካለ የችግሩ መንስዔ የሆነውን ሁኔታ መገንዘብ ያሻል።
  ትላንት ‘ኢትዮጵያዊ ማንነት’ ሲባል የኣንድ ብሄር እሴቶች ፍጹም የበላይነት የነገሰበት ማንነትን እያንጸባረቁ ሌሎች ህዝቦች እስከነመፈጠራቸውም ተረስተውና እንዲረሱም ሲደረጉ ነበር። ያ ለዘመናት የዘለቀው የጭፍን ጥላቻና ‘ኢትዮጵያዊ እኔ የሳልኩት ነው’ ኣስተሳሰብ ዛሬ በትውልድ መስዋዕትነት ተቀብሯል። ሆኖም ግን መንፈሱ የሚያቃዣቸው – በድን ፍጡራን ልበላቸው – ኣልታጡም።
  ስለኦሮሞ ማንነት ሲነሳ ኣልያም ኣንድ ግለሰብ እኔ ኦሮሞ ነኝ ካለ ወይንም የኦሮሞን ማንነት የሚገልጽ ድርጊት ከፈጸመ ኢትዮጵያ ልትጠፋ ነውና እንታደጋት በሚል ለዘመቻ ምላሽ ይሾላል፣ ከተቻለም ሌላም እኩይ ድርጊት ሲታሰብ ይስተዋላል።
  በተቃራኒው ደግሞ ማንነታቸው(ኦሮሞም ሆነ ሌሎች) እንደትላንቱ ማንነታችሁን እኛ እንንገራችሁ በሚሉ በእብሪተኞች እንዳይታፈን የሚሹት ስለእውነታው ድምጻቸውን ከፍ ኣድርገው ታሪኬ፣ ሃገሬና ማንነቴ ይኸ ነው ይላሉ።

  ኣስተያየቴን ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት የጋራ ማንነት ይገነባል? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ያለኝን መላሽ በመስጠት ልቋጭ። በ’ሃገሪቷ’ ያሉ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ማንነት ያለተቀበለ የጋር ማንነት መገንባት ጉም እንደመጨበጥ ነው። ህዝቦቹ ተስማምተውበት እኛ ይህ ነን ማለት መቻል ኣለባቸው- በኣንድ ወገን ይህ ናችሁ መባል የለባቸውም።

  የጋራ ኣስተሳሰብ ሲኖር የጋራ መስማማት ላይ ሊደረስ ይችላልና ከዚያም የጋራ ማንነትን ወደ መገንባት መሸጋግረ ያስችል ይሆናል – የሚያስተሳስራቸው ኣልያም የሚያስማማቸው ሁኔታ ከተፈጠረ ማለት ነው። ከሌለ ደግሞ እንዳልተስማሙ ተስማምተው በሰላም መለያየት። መቼም ይህችን መለያየት የሚሏትን ቃል ሲሰሙ የኢትዮጵያ ‘ተቆርቋሪዎች’ ወዴት-ወዴት! እንደሚሉ ይገባኛል። ሆኖም ግን ያለው እውነታ ይህ ነው። ስለሆነም የኦሮሞን ማንነት ኦሮሞ እራሱን እንደሚገልጸውና እውነታውም እንደሚያሳየው መቀበል ቢያንስ በ‘ሃገሪቷ’ የጋራ መግባባት በመድረሱ ሂደት የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን ይችላል። እንድ ነጥብ ላስምርበት ኦሮሞም ሆነ ሌሎች ህዝቦች እኔ እንዲሉ ነጻ ሲሆኑ(ሲፈቀድላቸው ኣላልኩም – ፈቃጅና ኣስፈቃጅ መኖር ስለሌለበት) ነው እኛ ወደማለቱ ኣስተሳሰብ የሚሻገሩት። የኦሮሞ ዜጋ ኦሮሞነትን ኦሮሞነትን በሚፈሩትና ከዚያም ኣልፈው ኣጥፍተው እነሱ ለኦሮሞ በፈጥሩት(‘ኢትዮጵያዊ’) ማንነት እንዲተካ ከሚባዝኑ የቀን ህልመኞች ጋር የሚገነባው የጋራ ማንነት ኣይኖርም።
  ኦሮሞ ማንም ወደድም-ጠላም ማንነቱ ነው፡ ኦሮሞነት(Oromummaa)። ኦሮሞነት እንደሆነም ይዘልቃል። ይህ ‘ለኢትዮጵያዊ ማንነት እንሰራለን’ እንደሚሉት ኣካላት ፉከራ ወይንም ኣስፈራሪያ ኣይደለም፡ እውነታ እንጂ! ተፈጥሮ የለገሰኝ የማንነቴ ኣሻራ!!!
  የትላንቱ የ’ኣንድነት’ ቀረርቶ ከቆሮኣችሁ ላይ ለሚያፏጭ፡ በጭፍን የብሄራዊ ማንነት ጥላቻ መንፈስ ለተለከፋችሁና ኦሮሞ ሲባል ለሚያጥወለውላችሁ ‘ሰዎች’ እነሆ ስጦታዬ!—- እኔ ኦሮሞ ነኝ! ኣዎን! ህዝቤ ኦሮሞ- ብሄሬ ኦሮሞ- ማንነቴ ኦሮሞነት — በብሄራዊ ማንነቴ የምኮራና ሌላውም በማንነቱ እንዲኮራበት የምሻ የኦሮሚያ ልጅ ነኝ ብያለሁ! የያዛችሁ እርኩስ መንፈስ ይዟችሁ እንጦሮጦስ ይውረድ!!!! ኣሜን! ኣትሉም

 8. ከሁሉም በፊት ስለኦሮሞ ማንነት ሲነሳ ኣንዳንዶች ኩራት ሲሰማቸውን ውስጣቸው በደስታ ሲሞላ ሌሎች ደግሞ እርር-ድብን ብለው መንጨርጨራቸውና የስድብ ናዳ ላማውረድ ሲጣደፉ መስተዋሉ ከበስተጀርባው ሚስጢር ስለመኖሩ ያመለክታል።

  ስለኦሮሞነት ለመናገርና የኦሮሞን ማንነት ለመግለጽ ከ’ኢትዮጵያዊነት’ ጎራ ፈቃድ ኣልያም ቡራኬ የሚያስፈልግ ኣይመስለኝም።
  የኦሮሞ ህዝብ በማንነቱ መገለጫ እሴቶች እንደሚኮራ ሁሉ ሌላውም ብሄር፡ ህዝብ ስለማንነቱ ኣንገቱን ቀና ኣድርጎ ቢናገርና ቢያንጸባርቅ ሊያንጨረጭረን ኣይገባም። በኣንጻሩ ያቺን ‘ሃገር’ ከገባችበት ኣጣብቂኝ ለማላቀቅና በውስጧ ያሉ ህዝቦች በሁሉም ኣንጻር ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ምኞትና ፍላጎቱ ያለው ካለ የችግሩ መንስዔ የሆነውን ሁኔታ መገንዘብ ያሻል።

  ትላንት ‘ኢትዮጵያዊ ማንነት’ ሲባል የኣንድ ብሄር እሴቶች ፍጹም የበላይነት የነገሰበት ማንነትን እያንጸባረቁ ሌሎች ህዝቦች እስከነመፈጠራቸውም ተረስተውና ማንነታቸውን እንዲረሱም ሲደረጉ ነበር። ያ ለዘመናት የዘለቀው ዘመቻ፦ የጭፍን ጥላቻና ‘ኢትዮጵያዊ እኔ የሳልኩት ነው’ ኣስተሳሰብ ዛሬ በትውልድ መስዋዕትነት ተቀብሯል። ሁሉም እኔ እና እኛን ኣልፎም እነርሱን ኣሳምሮ ለይቶ ያውቃል፡ ከኣውቆ ኣበዶች በስተቀር። ሆኖም ግን ያ የትላንቱ የእብሪት መንፈስ የሚያቃዣቸው ዛሬም ኣልታጡም።

  ስለኦሮሞ ማንነት ሲነሳ ኣልያም ኣንድ ግለሰብ እኔ ኦሮሞ ነኝ ካለ ወይንም የኦሮሞን ማንነት የሚገልጽ ድርጊት ከፈጸመ ኢትዮጵያ ልትጠፋ ነውና እንታደጋት በሚል ለዘመቻ ምላሽ ይሾላል፣ ከተቻለም ሌላም እኩይ ድርጊት ሲታሰብ ይስተዋላል።
  በተቃራኒው ደግሞ ማንነታቸው(ኦሮሞም ሆነ ሌሎች) እንደትላንቱ ማንነታችሁን እኛ እንንገራችሁ በሚሉ በእብሪተኞች እንዳይታፈን የሚሹት ስለእውነታው ድምጻቸውን ከፍ ኣድርገው ታሪኬ፣ ሃገሬና ማንነቴ ይኸ ነው ይላሉ።

  ኣስተያየቴን ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት የጋራ ማንነት ይገነባል? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ያለኝን መላሽ በመስጠት ልቋጭ። በ’ሃገሪቷ’ ያሉ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ማንነት ያለተቀበለ የጋር ማንነት መገንባት ጉም እንደመጨበጥ ነው። ህዝቦቹ ተስማምተውበት እኛ ይህ ነን ማለት መቻል ኣለባቸው- በኣንድ ወገን ይህ ናችሁ መባል የለባቸውም።

  የጋራ ኣስተሳሰብ ሲኖር የጋራ መስማማት ላይ ሊደረስ ይችላልና ከዚያም የጋራ ማንነትን ወደ መገንባት መሸጋግረ ያስችል ይሆናል – የሚያስተሳስራቸው ኣልያም የሚያስማማቸው ሁኔታ ከተፈጠረ ማለት ነው። ከሌለ ደግሞ እንዳልተስማሙ ተስማምተው በሰላም መለያየት። መቼም ይህችን መለያየት የሚሏትን ቃል ሲሰሙ የኢትዮጵያ ‘ተቆርቋሪዎች’ ወዴት-ወዴት! እንደሚሉ ይገባኛል። ሆኖም ግን ያለው እውነታ ይህ ነው። ስለሆነም የኦሮሞን ማንነት ኦሮሞ እራሱን እንደሚገልጸውና እውነታውም እንደሚያሳየው መቀበል ቢያንስ በ‘ሃገሪቷ’ የጋራ መግባባት በመድረሱ ሂደት የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን ይችላል።

  ኣንድ ነጥብ ላስምርበት፦ ኦሮሞም ሆነ ሌሎች ህዝቦች እኔ እንዲሉ ነጻ ሲሆኑ(ሲፈቀድላቸው ኣላልኩም – ፈቃጅና ኣስፈቃጅ መኖር ስለሌለበት) ነው እኛ ወደማለቱ ኣስተሳሰብ የሚሻገሩት። የኦሮሞ ዜጋ ኦሮሞነትን ኦሮሞነትን በሚፈሩትና ከዚያም ኣልፈው ኣጥፍተውት እነሱ ለኦሮሞ በፈጥሩት(‘ኢትዮጵያዊ’) ማንነት እንዲተካ ከሚባዝኑ የቀን ህልመኞች ጋር የሚገነባው የጋራ ማንነት ኣይኖርም።
  ኦሮሞ ማንም ወደድም-ጠላም ማንነቱ ነው፡ ኦሮሞነት(Oromummaa)። ኦሮሞነት እንደሆነም ይዘልቃል። ይህ ‘ለኢትዮጵያዊ ማንነት እንሰራለን’ እንደሚሉት ኣካላት ፉከራ ወይንም ማስፈራሪያ ኣይደለም፡ እውነታ እንጂ!

  የትላንቱ የ’ኣንድነት’ ቀረርቶ ከቆሮኣችሁ ላይ ለሚያፏጭ፡ በጭፍን የብሄራዊ ማንነት ጥላቻ መንፈስ ለተለከፋችሁና ኦሮሞ ሲባል ለሚያጥወለውላችሁ ‘ሰዎች’ እነሆ ስጦታዬ!—- እኔ ኦሮሞ ነኝ! ኣዎን! ህዝቤ ኦሮሞ- ብሄሬ ኦሮሞ- ማንነቴ ኦሮሞነት — ተፈጥሮ የለገሰኝ የማንነቴ ኣሻራ!!! በብሄራዊ ማንነቴ የምኮራና ሌላውም በማንነቱ እንዲኮራበት የምሻ የኦሮሚያ ልጅ ነኝ ብያለሁ! የያዛችሁ እርኩስ መንፈስ ይዟችሁ እንጦሮጦስ ይውረድ!!!!

  ኣሜን! ኣትሉም

 9. ከሁሉም በፊት ስለኦሮሞ ማንነት ሲነሳ ኣንዳንዶች ኩራት ሲሰማቸውን ውስጣቸው በደስታ ሲሞላ ሌሎች ደግሞ እርር-ድብን ብለው መንጨርጨራቸውና የስድብ ናዳ ላማውረድ ሲጣደፉ መስተዋሉ ከበስተጀርባው ሚስጢር ስለመኖሩ ያመለክታል።

  ስለኦሮሞነት ለመናገርና የኦሮሞን ማንነት ለመግለጽ ከ’ኢትዮጵያዊነት’ ጎራ ፈቃድ ኣልያም ቡራኬ የሚያስፈልግ ኣይመስለኝም።

  የኦሮሞ ህዝብ በማንነቱ መገለጫ እሴቶች እንደሚኮራ ሁሉ ሌላውም ብሄር፡ ህዝብ ስለማንነቱ ኣንገቱን ቀና ኣድርጎ ቢናገርና ቢያንጸባርቅ ሊያንጨረጭረን ኣይገባም። በኣንጻሩ ያቺን ‘ሃገር’ ከገባችበት ኣጣብቂኝ ለማላቀቅና በውስጧ ያሉ ህዝቦች በሁሉም ኣንጻር ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ምኞትና ፍላጎቱ ያለው ካለ የችግሩ መንስዔ የሆነውን ሁኔታ መገንዘብ ያሻል።

  ትላንት ‘ኢትዮጵያዊ ማንነት’ ሲባል የኣንድ ብሄር እሴቶች ፍጹም የበላይነት የነገሰበት ማንነትን እያንጸባረቁ ሌሎች ህዝቦች እስከነመፈጠራቸውም ተረስተውና ማንነታቸውን እንዲረሱም ሲደረጉ ነበር። ያ ለዘመናት የዘለቀው ዘመቻ፦ የጭፍን ጥላቻና ‘ኢትዮጵያዊ እኔ የሳልኩት ነው’ ኣስተሳሰብ ዛሬ በትውልድ መስዋዕትነት ተቀብሯል። ሁሉም እኔ እና እኛን ኣልፎም እነርሱን ኣሳምሮ ለይቶ ያውቃል፡ ከኣውቆ ኣበዶች በስተቀር። ሆኖም ግን ያ የትላንቱ የእብሪት መንፈስ የሚያቃዣቸው ዛሬም ኣልታጡም።

  ስለኦሮሞ ማንነት ሲነሳ ኣልያም ኣንድ ግለሰብ እኔ ኦሮሞ ነኝ ካለ ወይንም የኦሮሞን ማንነት የሚገልጽ ድርጊት ከፈጸመ ኢትዮጵያ ልትጠፋ ነውና እንታደጋት በሚል ለዘመቻ ምላሽ ይሾላል፣ ከተቻለም ሌላም እኩይ ድርጊት ሲታሰብ ይስተዋላል። በተቃራኒው ደግሞ ማንነታቸው(ኦሮሞም ሆነ ሌሎች) እንደትላንቱ ማንነታችሁን እኛ እንንገራችሁ በሚሉ በእብሪተኞች እንዳይታፈን የሚሹት ስለእውነታው ድምጻቸውን ከፍ ኣድርገው ታሪኬ፣ ሃገሬና ማንነቴ ይኸ ነው ይላሉ።

  ኣስተያየቴን ኦሮሞነትን የፈራ ኢትዮጵያዊነት እንዴት የጋራ ማንነት ይገነባል? በሚል ለቀረበው ጥያቄ ያለኝን መላሽ በመስጠት ልቋጭ። በ’ሃገሪቷ’ ያሉ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ማንነት ያለተቀበለ የጋር ማንነት መገንባት ጉም እንደመጨበጥ ነው። ህዝቦቹ ተስማምተውበት እኛ ይህ ነን ማለት መቻል ኣለባቸው- በኣንድ ወገን ይህ ናችሁ መባል የለባቸውም።

  የጋራ ኣስተሳሰብ ሲኖር የጋራ መስማማት ላይ ሊደረስ ይችላልና ከዚያም የጋራ ማንነትን ወደ መገንባት መሸጋግረ ያስችል ይሆናል – የሚያስተሳስራቸው ኣልያም የሚያስማማቸው ሁኔታ ከተፈጠረ ማለት ነው። ከሌለ ደግሞ እንዳልተስማሙ ተስማምተው በሰላም መለያየት። መቼም ይህችን መለያየት የሚሏትን ቃል ሲሰሙ የኢትዮጵያ ‘ተቆርቋሪዎች’ ወዴት-ወዴት! እንደሚሉ ይገባኛል። ሆኖም ግን ያለው እውነታ ይህ ነው። ስለሆነም የኦሮሞን ማንነት ኦሮሞ እራሱን እንደሚገልጸውና እውነታውም እንደሚያሳየው መቀበል ቢያንስ በ‘ሃገሪቷ’ የጋራ መግባባት በመድረሱ ሂደት የመጀመሪያው እርምጃ ሊሆን ይችላል።

  ኣንድ ነጥብ ላስምርበት፦ ኦሮሞም ሆነ ሌሎች ህዝቦች እኔ እንዲሉ ነጻ ሲሆኑ(ሲፈቀድላቸው ኣላልኩም – ፈቃጅና ኣስፈቃጅ መኖር ስለሌለበት) ነው እኛ ወደማለቱ ኣስተሳሰብ የሚሻገሩት። የኦሮሞ ዜጋ ኦሮሞነትን ኦሮሞነትን በሚፈሩትና ከዚያም ኣልፈው ኣጥፍተውት እነሱ ለኦሮሞ በፈጥሩት(‘ኢትዮጵያዊ’) ማንነት እንዲተካ ከሚባዝኑ የቀን ህልመኞች ጋር የሚገነባው የጋራ ማንነት ኣይኖርም።
  ኦሮሞ ማንም ወደድም-ጠላም ማንነቱ ነው፡ ኦሮሞነት(Oromummaa)። ኦሮሞነት እንደሆነም ይዘልቃል። ይህ ‘ለኢትዮጵያዊ ማንነት እንሰራለን’ እንደሚሉት ኣካላት ፉከራ ወይንም ማስፈራሪያ ኣይደለም፡ እውነታ እንጂ!

  የትላንቱ የ’ኣንድነት’ ቀረርቶ ከቆሮኣችሁ ላይ ለሚያፏጭ፡ በጭፍን የብሄራዊ ማንነት ጥላቻ መንፈስ ለተለከፋችሁና ኦሮሞ ሲባል ለሚያጥወለውላችሁ ‘ሰዎች’ እነሆ ስጦታዬ!—- እኔ ኦሮሞ ነኝ! ኣዎን! ህዝቤ ኦሮሞ- ብሄሬ ኦሮሞ- ማንነቴ ኦሮሞነት — ተፈጥሮ የለገሰኝ የማንነቴ ኣሻራ!!! በብሄራዊ ማንነቴ የምኮራና ሌላውም በማንነቱ እንዲኮራበት የምሻ የኦሮሚያ ልጅ ነኝ ብያለሁ! የያዛችሁ እርኩስ መንፈስ ይዟችሁ እንጦሮጦስ ይውረድ!!!! ኣሜን! ኣትሉም

 10. በገዛ ፍቃዳችን የወያኔ አሻንጉሊት ስንሆን እየታያችሁ ነው ግን? በቃ ወያኔ እኮ ይሄን ነው የሚፈልገው። ሰለልዩነት አስበን ያማናውቀውን ልዩነት እንዳለን እየሰበከ አሳድጎ ዛሬ ለዚህ አደረሰን። እኛ በዚህ ስንጨቃጨቅ የወያኔ ውጥረት በብዙ ይቀንሳል። የኛ አለመስማማት ለሱ ይጠቅመዋል። እባካችሁ ነቁ፤ በቁማችሁ እየሞታችሁ ነው እኮ። የሄ እኮ የሚያጨቃጭቅ ነገር አልነበረም። ዳሩ ግን ያልታደለ ትውልድ ባልሆነ ግዜ ተወልዷልና ይሄ ሆነ እድላችን። ደግሞ ብሄር ማለት ሃገር ማለት ነው እሺ፣ ብሄራዊ ባንዲራ፤ ብሄራዊ ቡድን ሲባል አታውቁም??

Leave a comment.

Your email address will not be published. Required fields are marked*