Dambal Galaana

teachersየ 2001 የአሸባሪዎችን ጥቃት ተከትለው የወቅቱ የአሜሪካው ፕ/ት ጆርጅ ቡሽ ለዓለም ሀገሮች ሁለት አማራጮችን አቅርቦ ነበር: “ወይ ከኛ ጋር ሁኑ ወይ ከአሸባሪዎች ጋር ሁኑ” የሚለው ምርጫ:: ሁሉም ሀገራት ማለት በሚቻል መልኩ የመጀመሪያውን ምርጫ መርጠው “አይ እኛ ከናንተ ጋር ነን” ነበር ያሉት:: በወቅቱ ትኩረትን ስቦ የነበረው የኢትዮጲያና የኤርትራ ጉዳይ ነበር:: እነዚህ ሚስኪን ሀገሮች አሜሪካ አፍጋንታንና ኢራቅን ለማጥቃት የእነሱን የአየር ክልል የሚያስፈልጋት ይመስል “አሜሪካ የአየር ክልላችን እንድትጠቀም ፈቅደናል” ነበር ያሉት::

አሁን በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን ተቀውሞ ተከትለው አንዳንድ ሰዎች ፕ/ት ቡሽ ለዓለም መንግስታት የቀረቡተን ምርጫ አይነት ለኢትዮጲያውያን እያቀረቡ ይገኛሉ: “ወይ ከኛ (#OromoProtests) ጋር መሆን ወይ ከገዳዮች ጋር መሆን::” በእኔ አመለካከት ግን እነዚህ አማራጮች በጣም ስለጠበቡ ሶስተኛ አማራጭ ጨምራው “ወይ ከኛ ጋር ሁኑ ወይ ከእነሱ ጋር ሁኑ ወይ ዝም በሉ” ማለት የሚሻል ይመስለኛል:: ከሶስቱ መሆን አቅቶት አንዴ እዚህ አንዴ እዚያ የሚሆን ሰው ካለ ደግሞ እኛ በኦሮሚኛ ጠወልዋሌ እንለዋለን:: እንደዚህ መሆን ደግሞ ጥሩ አይደለም::

ግን የኦሮሞን ህዝብ ንቅናቄን ወደ “ኢትዮጲያ” ህዝብ ንቅናቄ ለመለወጥ ለሚፈልጉ ወገኖች የሚለው ነገር አለኝ::ስርዓቱ አሁን እየተናቃነቀ ያለ ጥርስ ነው:: የተነቃነቀ ጥርስ ለባለቤቱም አይመችም:: ተስፋ የሚጣልበት አይሆንም ምክንያቱም አይበላበትም አይጠጣበትም:: በጣም ያማል:: ስለዚህ የተነቀነቀ ጥርስ መውለቁ አይቀርም:: ይሄን የስርዓቱን ሀይል እየነቃነቀ ያለው ደግሞ የኦሮሞ ወንዶች: ሴቶች: ወጣቶችና አረጋውያን ናቸው:: የኦሮሞ ሀቅ ነው:: የኦሮሞ መሬት ነው:: ለዘመናት ስደርስበት የነበረው የግፍ ዋጋ ነው::

አንዳንድ ኢትዮጲያዊያን ወገኖች ይሄንን በኦሮሞ ልጆች የተጀመረውን ትግል ለመቀላቀል ምክንያት በመፈለግ ላይ መሰንበታቸው ይታወቃል:: ሁለት ወር ያለፈውን ትግል ለመቀላቀል እስከ አሁን ምንም ምክንያት ያለማግኘቸው ግን የሚገርም ነው:: ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ ትግሉን ለመቀላቀል ምክንያት መጥፋቱ ብቻ ሳይሆን ላለመቀላቀልም ጭምር ምክንያት መጥፋቱ ነው::

በኔ አመለካከት ኦሮሞን ለተቃውመው ያነሱት ምክንያቶች ሌሎችም ጋር በሽበሽ ናቸው:: ልክ እንደ ኦሮሞሁሉ ሌሎችም መሬታቸውን ተነጥቀዋል:: ጋምቤላው: አፈሩ: ሶማሌው:ቤንሻንጉሉ: ሲዳማው: አማራው: ደቡቡ እና ሁሉም መሬቱን ተቀምተዋል:: በተለይ ከኦሮሞ ቀጥለው ብዙ ህዝብ ያለው አማራ ጣናን ከነኩራቱ አላጣም? አባይን ከነሞገሱ አላጣም? ዋልድባን ከነእምነቱ አልተነጠቀም? የጎንደር መሬት ከነወንዞቹ አልተወሰደበትም? ወልቃይት ጠገዴን መሬት ከነህዝቡ አልተቀማም ወይ? ይሄ ከመሬት ነጠቃም አልፎ የዘር ቅሚያ አይደለም እንዴ? እንግድህ ይህ ሁሉ “#OromoProtests”ን ለመደገፍ ምክንያት ካልሆነ ሌላ ምክንያት ከየት ይመጣል ታድያ?

አንዳንድ የዋህ ወገኖች ሌላው የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይ የአማራው መህበረሰብ ይህን ትግል ያልተቀላቀለው “የኦሮሞ ትግል ኢትዮጲያዊ ባህሪ የለውም” ብለው ይናገራሉ:: በመጀመሪያ “ኢትዮጲያዊ ባህሪ” ሲሉ ራሱ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግልፅ አይደለም:: “ኢትዮጲያዊ ባህሪ” ማለታቸው ሁሉን አቀፍ ወይም አገር አቀፍ ወይም “ኢትዮጲያዊ” አልሆነም ማለታቸው ከሆነ ግን መፍትሔው ሁለት ነው:: አንደኛው መፍትሔ የኦሮሞ ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተቀብለውና ደግፈው ትግሉን መቀላቀል ነው:: ይህ ከሆነ ሁሉንም መህበረሰብ ስላሚያሳትፍ ትግሉ ተውደደም ተጠላም የግድ “እትዮጲያዊ” ይሆናል:: ሁለትኛው መፍትሔ ደግሞ ልክ የኦሮሞ ህዝብ የራሱን ጥያቄ እንዳነሳ ሁሉም የራሱን ጥያቄ ማንሳት ያስፈልጋል:: ለምሳሌ የኦሮሞ ህዝብ የማስተር ፕላኑን የገበሬዎችን ማፈናቀል ጥያቄ አንስቶ ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ አማራውም ስለጎንደር መሬት ስለዋልድባና ስለወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ አንስቶ ሰላማዊ ሰልፍ ቢወጣ ትግሉ የተለያዩ የአገሪቱን ክፍሎች ስላሚያዳርስ አገራዊ ወይም “ኢትዮጲያዊ” ይሆናል ማለት ነው::

4 thoughts on “የኦሮሞ ህዝብ ትግል ወይስ የኢትዮጲያ ህዝብ ትግል?

 1. My Oromo fathers, mothers, brothers and sisters keep pushing. Please, don’t waste your time on so and so ethnic group is not with us. As the Oromo people, we can destroy the TPLF alone. We are like oxygen in the Ethiopian Empire. Keep pushing with confidence.

 2. Dear all,

  If a few of us believe Oromos struggle to get rid of woyanes/TPLF is that of Oromos only, I think we are making a serious mistake. It will be a repeat of Shabia’s and woyanes/TPLF claim.

  These two mercenary groups claimed that they crushed the Ethiopian people militarily. They may have won the war over the unpopular “Socialist Military Junta” or Derg, but not over the Ethiopian people. There is big difference between being victorious over the Ethiopian people and Mengistu Haile Mariam’s regime.

  Here is why Shabia’s and Woyanes/TPL’s claim was/is fabricated and wrong:

  First of all, there was no ethnic group that did not fight Derg directly or indirectly. We all did. It is only Shabia, woyanes/TPLF and their lovers that deny that.

  Second of all, the east block that supported Derg collapsed and thus the collapse of Derg regime at the same time. It will be history repeating if American and other western countries withdraw their support for woyanes/TPLF. See what I mean?

  Third of all, Derg killed several more army generals and high ranking military officers than Shabia and woyanes/TPLF combined. This was an indirect victory for Shabia and woyanes/TPF, but a moral collapse for the military. While the two mercenary bunch celebrated, the military was disbanded and the rest is history.

  As Oumar Hussein put it, “let us not waste our time on so and so ethnic group is not with us”. In other words, let us fight the fight. We like it or not, Oromos have taken the “lead” of the struggle. This means, Oromos are everywhere, they are the majority with the largest land mass.

  With this in mind, I would like to repeat what I said before several times. “There was no Ethiopia in the past without Oromos and there will never be one in the future”. That is my stand and how I see it.

  May God/Allah give us the wisdom and courage to do the right thing for our people and country?

  The struggle continues!!! We shall over come!!!

Leave a comment.

Your email address will not be published. Required fields are marked*