#OromoProtests Qobbo town in East Hararge still remains under military rule
#OromoProtests Qobbo town in East Hararge still remains under military rule


today1
የጋምቤላን ሕዝብ በደቡብ ሱዳን ኑኤር ቅጥረኞች ማስጨፍጨፍ ለምን ኣስፈለገ !? ጋምቤላ እንዲህ ነች !!!
#Ethiopia #Gambella #MinilikSalsawi #EPRDF #SouthSudan #Freedom

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኣሁን ወቅት በጋምቤላ ክልል የክልሉ መስተዳደር ስልጣን የሌለው ሲሆን የክልሉ ፖሊስ ሙሉ በሙሉ ማት ይቻላል ትጥቁን ፈቶ ይገኛል ሕዝቡ ተበታትኖ የሚገባበት ጠፍቶታል በጋምበላ ክልል የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከሕወሓት ዘራፊ ኢንቨስተር ተብየዎች ውጪ ሁሉም ሕዝብ ማለት ይቻላል ሕወሓት በፈጠረው የጎሳ ግጭት እና ሽብር የተነሳ ወደ ኣጎራባች ኣከባቢዎች ቤቱን ዘግቶ እየሄደ ነው።

ኣጎራባች ኣከባቢዎችን የሕወሓት ቅጥረኞች የውጡልን ቅስቀሳ ሊጀመር ይችላል የሚል የከፋ ስጋት ኣለ፤ጋምቤላን ህገመንግታዊ ዋስትና የሚያሳጣበትና የበለጠ ስርዓት አልበኝነትን ሚያሰፍንበት ስልት መሆኑ ነዉ በሕወሓቶች ተነድፎ በቤተሰቦቻቸው እና በቢዝነስ ኣጋሮቻቸው የተወረረውን የጋምብትትላ ሕዝቦች መሬት በህዝቡ እንዳይነጠቅ ሕዝቡ መሬታችንን የሚል ጥያቄ እንዳያነሳ በኣግኣዚ ጦር ኣከባቢውን በማስወረር እና ቅጥረኛ የደቡብ ሱዳን ኑኤሮችን በማስታጠቅ ሕዝቡ ላይ ዘምቶ በመግደል እና በማቁሰር ክልሉ መንግስት ኣልባ የደቡብ ሱዳን ወንበዴዎችና የኣግኣዚ ገዳይ ወታደሮች መፈንጫ ኣድርጎታል።ከዝቅተኛ ምስኪን የጋምቤላ ነዋሪ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣን ተገድለዋል፥ግድያው የሚከናወነው በኣግኣዚ ወታደሮች ትብብር\እገዛ ከደቡብ ሱዳን ፈልሰው በገቡ የኑኤር ተወላጆች መሆኑ አጅግ ኣስደንጋጭ ነው።

ጋምቤላ ይህን ትመስላለች እንግዲህ በኣከባቢው ሁኔታውን አያዩ ያሉ የክልሉ ባለስልጣናት እና ታዛቢ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች የሚናገሩት የተነሳው ችግር በቀላሉ የሚበርድ ኣይደለም። ቅጥረኞቹ የኣኝዋክ ሰዎችን ማጥራት እና ኣንገት ማስደፋት ኣለባቸው ኣስቸጋሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ኑኤሮችንም መምታት ይጠበቀባቸዋል ለዚህም ኣግ ኣዚ ሰራዊት ከጀርባቸው እየተከታተለ እገዛው ያደርግላቸዋል፤ የሕወሓቶች ይህንን እኩይ ድርጊት መፈጸም የመሬት እና የኮንትሮባንድ ስራዎችን እንዲሁም በኣከባቢው የሚገኙ የማእድን ስራዎችን እንደለመዱት በበላይነት ከክልሉ ተፈጥሮ ሃብት በመበዝበዝ ወደ ውጪው ኣለም በመላክ የሚያካብቱት ሃብት እንዳይጎልባቸው ሲሆን ይህንን ጸብ የጀመሩትም የተሳሳተ መረጃ ኣኘኣኮች ሃገራችንን ለቃቹ ውጡ እያሉ በሚል ለደቡብ ሱዳን ኑኤር ታጣቂዎች በመስጠት እንዲሁም በኣኝዋክ እና ኑኤር ተወላጆች መካከል የመረት ድንበር ጸብ እንዲነሳ በማድረግ በኣኝዋክ መሬቶች ላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ኑኤሮችን በማስፈር ነገሩ እንዲከር እና ተብላልቶ ለኣሁኑ ግድያ እና ጭፍጨፋ ኣቀባብለው ኣድርሰውታል።

የጋምቤላን ሕዝብ ማስጨፍጨፍ ያስፈለገው የኦሮሚያን ሕዝብ የመሬት ጥያቄ ተከትሎ በጋምቤላ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመድፈን በብዛት የጋምቤላ መሬቶች የተያዙት በሕወሓት እና ጋሻ ጃግሬዎች በመሆኑ በመሬቱ ላይ ኣደጋ እንዳይጠል እና በሕዝቡ እንዳይወረር በመፍራት ቀድመው ሕዝቡን በማሸበር ስርኣት ኣልበኝነት ያነገሱ ሲሆን በጋምቤላ ያላቸውን ንብረት በራሳቸው ሰራዊት በኣግኣዚ በማስጠበቅ ላይ ይገኛሉ ብተጨማሪም በምስራቅ የኢትዮጵያ ድንበር እንደለመዱት በደቡብ ሱዳን በኩል ባለው ድንበር ግምታቸው ከፍተኛ የሆነኑ የኮንትሮባንድ ንብረቶችን ስለሚያስገቡ ይህ ጉዳይ በክልሉ የፋይናንስ ቢሮ በኩል እርምጃ ሊወሰድበት ተጠንቶ ስላለቀ በተግባር ላይ ከዋለ ኣደገኛ በመሆኑ ከሁሉም ሳንቀደም እንቅደም በማለት ክልሉ ላይ ኣደጋ ኣዝንበውበታል።ተጨማሪ መረጃዎችእንደደርሱ ይቀጥላሉ።

Leave a comment.

Your email address will not be published. Required fields are marked*